ጳጉሜ 3 “የጽናት ቀን”

ለአንድ አገር ጽናት ማለት አገር ከውጭም ሆነ ከውስጥ የሚመጡ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ጸጥታዊ ጫናዎችንና ቀውሶችን ተቋቁማ ሉዓላዊነቷን፣ አንድነቷን እና ህልውናዋን አስጠብቃ መቀጠል የምትችልበት ኃይልና ማዕቀፍ ነው።

ብሔራዊ አንድነት እና ማኅበራዊ መስተጋብር መፍጠር፣ ጠንካራ የተቋማት አሠራር መኖር፣ ለፈተና የማይበገር ኢኮኖሚያዊ አውድ መፍጠር፣ ሉዓላዊነት እና ጸጥታን ማስከበር እንድሁም ፍትሃዊ ሀብት ክፍፍል እና መልካም አስተዳደር ማስፈን ደግሞ የአገር ጽናት መገለጫዎች እና ማጠናከሪያ ምሰሶዎች ናቸው።

በአጠቃላይ ስለአገር ጽናት ሲወራ ችግሮች ፈጽሞ አያጋጥሟትም ማለት ሳይሆን፣ ችግሮች ሲያጋጥሟት ከውድቀት ርብቃ ወጥታ በይበልጥ ጠንክራ የመውጣት አቅም ማዳበር ማለት ነው።

8 views 0 likes
Share Telegram WhatsApp