ጳጉሜ 4 “የህብር ቀን

ልዩነታችን_ውበታችን_ጥንካሬያችን_በአብሮነታችን_ላይ_ነው።
አገራችን ኢትዮጲያ የተለያዩ ቋንቋዎች፣ ባህሎች፣ ሃይማኖቶች፣ ጎሳዎች እና አመለካከቶች ያሉን ማህበረሰቦች በአንድነት ለዘመናት የኖርባት አገር ስትሆን፡ ስርአት ረዘም ያለውን ጊዜ በፍጹም አንድነት አንዱን ከፍ ሌላውን ዝቅ ያደረገበትን እና የተወሰነውን ጊዜ ደግም ፍጹም ልዩነት ኢትዮጵያዊነትን ችግር ውስጥ ያስገባበትን ፍጹም ተቃራኒ ጫፎች አሳልፈናል።

በሁለቱም የተለያዩ አላስፈላጊ ጫፎች ስርአት የጠቀመው ወይም የጎዳው ይኑር እንጅ ህዝቦቿ በፍጹም ህብረብሄራዊነት በአገራዊ አጀንዳዎች እኩል እየተሰለፉና እየሞቱ ኢትዮጵያን ከነስብራቷ ከትውልድ ትውልድ እያሸጋገሩ እዚህ አድርሰውናል።

አሁን ላይ ደግሞ በብልፅግና በመደመር ፍልስፍና ሁለቱንም ጫፎች የሚያስታርቅና የብቸኝነት ጉድለትን የሚሞላ ስርአት በመዘርጋት የብሄራዊነት ትርክ የሚያብብባትና ህዝቦቿ በህብር የሚኖሩባት ህብረብሄራዊት አገር በመገንባት ላይ እንገኛለን።

ይህ ስርአት ማህበራዊ ትስስራችንን የምናጠናክርበትን እና ባህላዊ ሃብታችንን ለአገር አንድነትና ብልጽግና የምንጠቀምበትን እድል በመፍጠር የጋራ ዕድገት ማረጋገጥ ያስችለናል።
🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 #ኢትዮጵያችን #ለዘላለም_ትኑር! 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹

9 views 0 likes
Share Telegram WhatsApp