“አርቆ ማየት፤ አልቆ መሥራት”

የደቡብ ወሎ ዞን አጠቃላይ አመራሮች የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ (ኦሬንቴሽን) መድረክ በደሴ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

ደሴ፣ መስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም (ደቡብ ወሎ ኮሙዩኒኬሽን)

«አርቆ ማየት፤ አልቆ መስራት» በሚል መሪ ቃል በደሴ ከተማ የተጀመረው ይህ መድረክ የፓርቲና የመንግሥት ሥራዎችን አፈጻጸም ለመገምገም ያለመ ነው። በስብሰባው ላይ ከዞኑ በተጨማሪ የ29 ወረዳዎች እና የከተማ አስተዳደሮች ጠቅላላ አመራሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ይህ አጠቃላይ የምክክርና የዕቅድ ትውውቅ መድረክ እስከ መስከረም 6 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ እንደሚቀጥል የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

*****

የደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ

ተደራሽ የሚያደርግባቸው አማራጮች ቀጣዮቹ አድራሻዎች ናቸው። ሊንኮቹን በመጫንና በመወዳጀት ፈጣንና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት ቤተሰባችን ይሁኑ\

22 views 0 likes
Share Telegram WhatsApp