የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ሽልማትና ዕውቅና ሰጠ

የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር በ2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ሽልማትና ዕውቅና ሰጠ

ደሴ፣ መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም (ደቡብ ወሎ ኮሙዩኒኬሽን) — “አርቆ ማየት፤ አልቆ ማሥራት” በሚል መሪ ሐሳብ በደሴ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የደቡብ ወሎ ዞን አጠቃላይ አመራሮች የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግሥት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ በስኬት ተጠናቋል።

የመድረኩን መጠናቀቅ ተከትሎ በበጀት ዓመቱ በትኩረት ዘርፎች የላቀ የሥራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የሽልማትና የዕውቅና መስጫ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በዚህም መሠረት፦

በወረዳዎች ደረጃ፦

1ኛ ደረጃ፦ ቃሉ ወረዳ (የሞተር ሳይክልና የዋንጫ ተሸላሚ)

2ኛ ደረጃ፦ ወረኢሉ ወረዳ (የሁለት ወተር ፓምፕና እውቅና ስርተፊኬት ተሸላሚ)

3ኛ ደረጃ፦ ወረባቦ ወረዳ (የአንድ ወተር ፓምፕና የዕውቅና ሰርተፊኬት ተሸላሚ)

በከተማ አስተዳደሮች ደረጃ፦

1ኛ ደረጃ፦ ሐይቅ ከተማ አስተዳደር (የሞተር ሳይክልና የዋንጫ ተሸላሚ)

2ኛ ደረጃ፦ ደጎሎ ከተማ አስተዳደር (የሁለት ወተር ፓምፕና የዕውቅና ሰርተፍኬት ተሸላሚ)

3ኛ ደረጃ፦ ጊምባ ከተማ አስተዳደር (የአንድ ወተር ፓምፕና የዕውቅና ሰርተፊኬት ተሸላሚ)

ይህ የተሰጠው ዕውቅናና ሽልማት በቀጣዩ የ2019 በጀት ዓመት የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና በየደረጃው ያሉ መዋቅሮችን ለበለጠ ስኬት ለማነሳሳት ያለመ መሆኑ ተገልጿል

31 views 0 likes
Share Telegram WhatsApp