የነገው ቀን

በደቡብ ወሎ ዞን«የነገው ቀን»ን ምክንያት በማድረግ በዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ አካሄደ
ደሴ፣ ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ.ም
“የነገው ቀን”;ን ምክንያት በማድረግ በዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በደሴ ከተማ ተካሄዷል፡፡
 
በመክፈቻው የደቡብ ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ ኃላፊ አቶ በሪሁን ተገኝ እንደተናገሩት «የነገው ቀን» በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተተገበሩ ያሉ የቴክኖሎጂ አማራጮች የሚዘከሩበት፣ ወደ ተግባር የሚገቡበት እና አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች እውቅና የሚያገኙበት መድረክ ነው።
ኃላፊው አክለው እንደገለጹት፤ ከተለመደው የአሰራር መንገድ በመውጣት አሰራሮችን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ማሸጋገር ወቅቱ የሚጠይቀው አስፈላጊ ጉዳይ ነው። በእጃችን የሚገኙ እንዲሁም ከበላይ አካላት የተላኩ በርካታ የቴክኖሎጂ አማራጮችን አቅም አውጥቶ በመጠቀም በወረዳና በዞን ደረጃ ማደራጀትና ማስፋፋት እንደሚገባም አሳስበዋል።
 
በወረዳ ደረጃ «የሞሰብ አንድ ማዕከል» አገልግሎትን ታሳቢ ያደረጉ ውይይቶች፣ ሴሚናሮችና ለሪፎርም ሥራው የሚያግዙ ልዩ ልዩ ኩነቶች ተካሂደዋል።
የዞኑ የ-ICT ባለሙያዎች አዳዲስ የቴክኖሎጂ ሀሳቦችን በማመንጨት በየተቋሞቻቸው እንዲተገብሩ፤ እንዲሁም ለአመራሩ በቂ ግንዛቤ በመፍጠር ሂደቱን በባለቤትነት እንዲመሩ ተልዕኮ ተሰጥቷቸዋል ነው ያሉት አቶ በሪሁን።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጁ የቴክኖሎጂ አማራጮችን በየተቋማቱ ለማስፋት የተዘጋጁ ሲስተሞች የቀረቡ ሲሆን፤ ባለሙያዎች ማስታወሻ በመያዝ ገንቢ ግብዓቶችንና ትችቶችን እንዲሰጡበት ተደርጓል።
በመድረኩ የዞኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላዎችና የመምሪያዎች የ-ICT ባለሙያዎች ናቸው የተሳተፉት፡፡

18 views 0 likes
Share Telegram WhatsApp