የግንባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ።

በቃሉ ወረዳ አንቻሮ ከተማ በማህበረሰብ ተሳትፎ ሁሉን አቀፍ ጤና ኬላ (Comprehensive Health post) ለመገንባት የግንባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ።

በቃሉ ወረዳ የእናቶችና ሕፃናትን ጤና ለማሻሻል፣ የአገልግሎት ተደራሽነቱንና ጥራቱን ለማሳድረግ የሚያስችል ሁሉን አቀፍ ጤና ኬላ በአንቻሮ ከተማ ለመገንባት የግንባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሂዷል።

በፕሮግራሙ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር አብዱ ሁሴን፣ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮንን፣ ሌሎች የክልል የዞንና የወረዳ አመራሮ፣ የአካባቢው ተወላጅ ባለሀብቶችና የአካባቢው ማህበረሰብ ተገኝተዋል።

8 views 0 likes
Share Telegram WhatsApp